News, Uncategorized, ታሪክ, ቴክኖሎጂ

“የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ጽንፈኞች ከሌሎች ኃይሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው” – ጀኔራል አሳምነው ፅጌ

ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ያደረገው ቆይታ:

ቢቢሲ፦ በቅርቡ በቅማንት ተወላጆች ላይ አማራ ክልል ውስጥ ጥቃት እየደረሰ ነው የሚሉ ዘገባዎች ይደመጣሉ። ስለዚህ ያለዎት መረጃ ምንድነው?

ጄነራል አሳምነው፦ የቅማንትና የአማራ ሕዝብ ለዘመናት አብሮ የዘለቀ ሕዝብ ነው። በብዙ ነገር የተሳሰረ ሕዝብ ነው፤ ሕብረተሰብ በሚያገናኙ እንደ ባህል እና ቋንቋ ባሉ እሴቶች የተሳሰረ ነው። ሰሞኑን የተፈጠረው ሁኔታ ቀደም ብሎ የተለያዩ ኃይሎች በተለያየ መንገድ የአካቢቢውን ሰላም ለመንሳትና አለመረጋጋቱ እንዲቀጥል ለማድረግ በፈጠሩት ሥራ የተፈጠረ ችግር ነው።
እንደ ሕዝብም ሆነ እንደ ተቋም ሲታይ፤ የቅማንት ሕዝብ በተለየ መንገድ ጥቃት የሚደርስበት ተጨባጭ ሁኔታዎች የሉም። ስለዚህ የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኛ ኃይሎች ከሌሎች ጋር በቅንጅት በመሥራት አካባቢው እንዲቃወስ ለማድረግ ሞከረዋል። ለምሣሌ በቅርቡ በተነሳው ግጭት ከአማራም፤ ከቅማንትም ሰዎች ሞተዋል። ቁጥሩ መጣራት ቢኖርበትም በአማራ በኩል የሞተው ያይላል። ይህ ጥቃትን ሳይሆን ግጭትን የሚያመለክት ነው። ነገር ግን ይህንን ለመጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎች ይኖራሉ። በገበሬ ደረጃ ሊያዙ የማይችሉ ትጥቆች ሁሉ ተገኝተዋል።
ከጎረቤት ሃገር ሊሆን ይችላል፤ ከጎረቤት አካባቢ ወይም ክልል ሊሆን ይችላል፤ ብቻ የቆየ ጥቅማቸውን ለማሳካት ‘ስትራቴጂ’ ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ያሉ አሉ።

ቢቢሲ፦ ብዙ ጊዜ የውጭ ኃይሎች፤ ሰላም የማይፈልጉ እና መሰል አገላለፆች አሉ። ነገር ግን ጣልቃ የሚገባ ኃይል አለ ተብሎ የሚታመን ከሆነ ለምን ስም መጥራት አልተፈለገም?

ጄነራል አሳምነው፦ እሱ ይጣራል። ይጣራል ብቻ ሳይሆን አደጋ እስከሆነ ድረስ ደግሞ ትግል ይካሄድበታል። በመረጃ የበለጠ አጠናክረን ይህንን ኃይል ማጋለጥም፤ መታገልም ይቻላል። ብቅ ብቅ የሚሉት መረጃዎች አንድ ላይ ‘ሰመራይዝ’ (ተጠቃለው) ፤ ከዚህ በኃል እየሆነ ያለው ነገር እናያለን።
ለምሳሌ ቅማንት 69 ቀበሌዎች እንዲያደራጅ ተፈቅዶለታል። ኃይሉ ይህ እንዲደራጅ አልፈለገም፤ የብጥብጥ ቀጠና እንዲሆን ነው የፈለገው። እነኚህ ኃይሎች ደግሞ ከጎረቤት ክልል የሚድያ ሽፋን ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ የዛሬ ሁለትና ሶስት ዓመት የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ከሰሞኑ እንደተደረጉ ተደርገው ይቀርባሉ። የሞተው ሌላ ሆኖ እያለ የሞተው ይሄ ነው ይባላል። ላሊበላ ላይ የደረሰ ግጭት እንደቅማንት ሆኖ ይቀርባል። እንዲህ ዓይነት ከእውነታ የራቀ መረጃ ይለቀቃል። ፌስቡክ ያለው ጥሩ ገፅታ እንዳለ ሆኖ መጥፎ የሆኑ መረጃዎች ይሰራጩበታል። ይህንን መረጃ ባትቀበሉት ጥሩ፤ ከተቀበላችሁት ደግሞ ብታጣሩት ደስ ይለኛል።

ቢቢሲ፦ ከጎረቤት ክልል ድጋፍ ይደረግላቸዋል የሚል ነገር ነግረውናል፤ የትኛው ክልል ይሆን?

ጄነራል አሳምነው፦ እሱን እነግርሃለሁ፤ በሂደት ብዬ ነው። እነርሱም ያውቁታል፤ እኛም እናውቀዋለን። ከእኔ ይበልጥ ሚድያ ላንተ ይቀርባል። ከኔ ልስማው ብለህ ካልሆነ በስተቀር ‘ዩ ኖው ኢት ቬሪ ዌል’ (በደንብ ታውቀዋለህ)፤ ይሄ በአደባባይ እየተሰራ ያለ ሥራ ስለሆነ። ነገሮች እየጠሩ ሲሄዱ መረጃዎችን አጠናክረን ለእናንተ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሚድያዎችም መረጃ እንሰጣለን።

ቢቢሲ፦ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ መተማ ውስጥ ያጋጠመ ችግር አለ። ለምሳሌ የቅማንት እና የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ተፈፅሟል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው። ስለዚህስ ያለዎት መረጃ አለ?

(Visited 48 times, 1 visits today)
November 8, 2018

About Author

admin


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

About Us

The Black Lion is a magazine and online media outlet focusing on the issues of Ethiopia and Ethiopian politics. To serve you best, we produce our journalism across a range of platforms, with a particular focus on politics, economy, culture, entertainment and new forms of storytelling. We’ve grown from a single Facebook page into a suite of digital products like website and into a newsletter.

Email: abcd@gmail.com

Logo