የአማራ ብሄር ተወላጆች ራሳችሁን ከማንኛውም ግጭት በማራቅ እርስ በርስ መረጃ በመለዋወጥ ራሳችሁን ትጠብቁ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁኝ። – Veronika Melaku
Opinion

የአማራ ብሄር ተወላጆች ራሳችሁን ከማንኛውም ግጭት በማራቅ እርስ በርስ መረጃ በመለዋወጥ ራሳችሁን ትጠብቁ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁኝ። – Veronika Melaku

አሳ ለመኖር የግድ ውሃ ያስፈልገዋል። የአሳ ህልውና የተመሰረተው በውሃ ነው። ዓሳን ከውሃ ውስጥ አውጥታችሁ ወደ የብስ ከወረወራችሁት ህልውናው ያበቃለታል።
ጃዋር የሚኖረው ግጭት ሲኖር ነው። የጃዋር ህልውና የተመሰረተው በግጭት ውስጥ ነው። በህዝብ መካከል ግጭት ጠፍቶ በአገር ላይ ሰላም ከወረደ የጃዋር የፖለቲካ ህይወት ያበቃለታል። ጃዋር የታወቀው ፣ ዝነኛ የሆነውና ሀብታም የሆነው ግጭትን በማራገብና በግጭት ላይ ዜና በመስራት ነው። ጃዋር ግጭትን እንደ ኦክስጅን ወደ ሳምባው በመማግ የሚኖር የግጭት ኢንተርፕሪዮኔር ነው። በዚህም መሰረት ጃዋር ይኖር ዘንድ ግጭትን መፍጠር አለበት። ጃዋር ግጭትን ለመፍጠር የሚያመች የደነቆረ አዙሮ የማያስብ መንጋ ተከታይ አለው። ጃዋር ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ክቡር የሰው ልጅ መገደል ይጀምራል ከአገር ሲወጣ ደሞ ሰላም ይሰፍናል።

ሰሞኑን አገሪቱን ወደ ትኩስ የግጭት ምእራፍ የሚያስገባ አደገኛ የእርስ በርስ ግጭት በብዙ ዩኒቨርሲቲዎች እየተለኮሰ እንደሆነ እየሰማን ነው። ግጭቱ መጀመሪያ የተጀመረው ጃዋር ደርሶ በተመለሰበት አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንደሆነ እየተሰማ ነው። በዚህም የአገር የነገ ተስፋ የሆኑ ተማሪዎች ህይወት ተቀጥፏል። በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲም ጠብ አጫሪ አደገኛ የኦሮሞ ተማሪዎችና ቄሮዎች የመማር ማስተማር ሂደቱን በማወክ በሌሎች ብሄር ተወላጆች በተለይም በአማራ ተማሪዎች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ እንደሆነ ተረጋግጧል። ግጭቱ ወደ ሌሎች ኦሮሚያ ውስጥ ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እየተስፋፋ እንደሆነ እየሰማን ነው።
.
የዚህ አደገኛ ጠብ ተንኳሾች የጃዋርና የኦነግ ተከታይ የኦሮሞ መንጋ ተማሪዎች እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። የሚያስገርመው ነገር ደሞ በክልላቸውም ሆነ ከክልላቸው ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የግጭቱ ጠንሳሾችና ዋና ተዋናዮች ከኦሮሞ ብሄር የተገኙ አንዳንድ በጥባጭ ተማሪዎች መሆናቸውን ነው።የጥቃቱ ሰለባዎች ደሞ የአማራ ተማሪዎች እንደሆኑ እየሰማን ነው። ይሄ በምንም መልኩ ተቀባይነት የለውም። ይሄን አይነት አፀያፊ ድርጊት በፍፁም አንታገስም።

መንግስት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ይሄን ነውር ማስቆምና የአደገኛ ወንጀሉን ፈፃሚዎች አቀጣጣዮች ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል። እየሞቱ መማር የሚባል ሂደት ስለሌለ መንግስት ይሄን የመማር ማስተማር ሰላማዊ ሂደት የሚያውኩ ጋጠወጦች አደብ ካላስገዛ በኦሮሚያ ክልል ዩኒቨርሲቲ ወስጥ የሚማሩ የአማራ ተማሪዎቻችንን ወደ ክልላቸው እንድመለሱ ጥሪ የምናደርግ መሆናችንን ሊሰመርበት ይገባል።
በዚህ አጋጣሚ የአማራ ብሄር ተወላጆች ራሳችሁን ከማንኛውም ግጭት በማራቅ እርስ በርስ መረጃ በመለዋወጥ ራሳችሁን ትጠብቁ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁኝ።

(Visited 9 times, 1 visits today)
November 21, 2018

About Author

admin


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

About Us

The Black Lion is a magazine and online media outlet focusing on the issues of Ethiopia and Ethiopian politics. To serve you best, we produce our journalism across a range of platforms, with a particular focus on politics, economy, culture, entertainment and new forms of storytelling. We’ve grown from a single Facebook page into a suite of digital products like website and into a newsletter.

Email: abcd@gmail.com

Logo