በየቦታዉ ያለ የአማራ ተማሪ ወደ አዲስ አበባ እና አማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች መመደብ አለበት፡፡ – Miky Amhara
Opinion

በየቦታዉ ያለ የአማራ ተማሪ ወደ አዲስ አበባ እና አማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች መመደብ አለበት፡፡ – Miky Amhara

በእየ አመቱ ለትምህርት ብለን በየ አካባቢዉ የላክናቸዉን ወንድሞች እና እህቶች ሬሳ እየተቀበልን የምንቀብርበት ጉዳይ የለም፡፡ አሶሳ ዩኒቨርስቲ ላይ የሞቱ ልጆች እንዳሉ ቴክስት እየደረሰኝ ነዉ፡፡ ሲጀምር ይሄ ክልል መንግስት አልባ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለምን ተማሪ እንደመደቡበትም አይታወቅም፡፡ ሲቀጥል ዩኒቨርስቲ ዉስጥ ተማሪ እስኪሞት ድረስ እንዴት የራሱ የግቢዉ ጸጥታ፤ የአካባቢዉ ፖሊስ የለም፡፡ እዛ ዩኒቨረስቲ ዉስጥስ ምንድን ነዉ ሰሞኑን ሲዶለት የነበረዉ??

አሁንም አስፈላጊዉን እርምጃ ካልተወሰደ አመቱን ሙሉ በዚህ ዩኒቨርስቲ እንዲህ ሆነ በዛ ዩኒቨርስቲ እንዲያ ሆነ፤ ይሄን ያህል ተገደሉ እየተባለ መቀጠላችን ነዉ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን የሚመድብበት መስፈርትም ግልጽ አይደለም፡፡ የአማራ ተማሪዎች ባብዛኛዉ ጠርፍ ጠርፍ ዩኒቨርስቲዎች ላይ ይመደባሉ፡፡ ይሄን ቢሮ የሚመራ ደግሞ አንድ አንቀልባ የሆነ ስሙን በትክክል የሚጽፍ እራሱ አይመስለኝም ጥላየ ጌጤ ሚባል አዛባ ነዉ፡፡ በእየ አመቱ በዬኒቨርስቲዎች ተማሪወች የሚሞቱበትን ምክንያት አያጣራ፤ አስፈላጊዉን እርምጃ አይወስድ እየሸፋፈነ እዚህ አድርሶታል፡፡ አሁን ላይ ደግሞ ሌላ ቢሮ ተገንጥሎ ተፈጥሯል መሰለኝ፡፡

አሁን መፍትሄዉ ሁሉም በየቦታዉ ያለ የአማራ ተማሪ ወደ አዲስ አበባ እና አማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች መመደብ ብቻ ነዉ፡፡ አሶሳ ላይ የተደረገዉ ነገር ተጣርቶ እርምጃ መወሰድ አለበት፡፡ አለበለዚያ ከአማራ ተማሪወች ማህበር ጋር ተመካክረን ሁሉም ወደ ቤቱ ሚመጣበትን መንገድ እናመቻቻለን፡፡ በአማራ ክልል ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ከአቅም በታች ነዉ ተማሪ የተቀበሉት፡፡ ብዙ ተማሪዎች በአካባቢያቸዉ መማር ፈልገዉ ግን እነዚህን ዩኒቨርስቲዎች የሚመሩ በሌብነት የተጨማለቁ ካድሬወች ከላይ አልታዘዝነም በማለት ይከለክላሉ፡፡እኒህን ተላላኪወች እራሱ ማጽዳት አለብን፡፡

(Visited 5 times, 1 visits today)
November 21, 2018

About Author

admin


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

About Us

The Black Lion is a magazine and online media outlet focusing on the issues of Ethiopia and Ethiopian politics. To serve you best, we produce our journalism across a range of platforms, with a particular focus on politics, economy, culture, entertainment and new forms of storytelling. We’ve grown from a single Facebook page into a suite of digital products like website and into a newsletter.

Email: abcd@gmail.com

Logo