ሌባ ሲታሰር ብሔርን መከላከያ ካደረጉት፣ ሌብነት ብሔር አለው ለማለት እንገደዳለን! – ጌታቸው ሽፈራው
Opinion

ሌባ ሲታሰር ብሔርን መከላከያ ካደረጉት፣ ሌብነት ብሔር አለው ለማለት እንገደዳለን! – ጌታቸው ሽፈራው

ሌባ ሲታሰር ብሔርን መከላከያ ካደረጉት፣ ሌብነት ብሔር አለው ለማለት እንገደዳለን!

ከሰረቁት መካከል እጅግ ጥቂቶቹ ለሕግ ሲቀርቡ “የብሔር ጥቃት ነው” ከተባለ እኛም ስልጣን ይዞ ከነበረው፣ ለመስረቅ ምቹ ሁኔታ ከነበረው፣ ለመዝረፍ ትልቅ አቅም ከነበረው አንፃር፣ ሲሰርቅ ደፍሮ “ተው” የሚለው ያልነበረውም አስበን “ሌብነት ብሔር አለው” ለማለት እንገደዳለን!

አዎ ብሔር ተገን ተደርጎ ተዘርፏል! አዎ በአንድ ብሔር ስም የመጡ ስልጣንን ተገን አድርገው ተሿሹመዋል። ሰርቀዋል። ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ሌላው እንዲሰርቅ ፈቃጅም ከልካይም ነበሩ። የሌላውን ሌባ ባለስልጣንም ይቀመጥ የነበረው በእነሱ ይሁንታና ይሁንታ ብቻ ነበር። ሌባን የሚፈቅዱለት ብቻ ሳይሆን ሆን ብለው የሚያስቀምጡት፣ የሚመለምሉት፣ በሌብነቱ የሚጠቀሙበት እነሱ ነበሩ።

አሸዋን ስኳር ነው ብሎ ሲያመጣ የነበረው ሳይታሰር፣ የስኳር ፋብሪካውን ያከሰረው ሳይታሰር አውሮፕላን ያጠፈው፣ ሀገር የዘረፈው አንዳንድ ሌባ በመታሰሩ ብሔሩ የሚጠቀስ ከሆነ፣ ዘራፊ ዘርፎም ወደብሔሩ ጎሬ የሚገባ ከሆነ “ሌብነት ብሔር አለው” ለማለት መሳቀቅ የለብንም!

አሁን ባለው ሁኔታ፣ ባለፈው 27 አመት ከተፈጠረው ሁኔታ ሌብነት ብሔር አለው! ወደኋላ ወደፊት አያስፈልገውም!

(Visited 1 times, 1 visits today)
November 21, 2018

About Author

admin


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

About Us

The Black Lion is a magazine and online media outlet focusing on the issues of Ethiopia and Ethiopian politics. To serve you best, we produce our journalism across a range of platforms, with a particular focus on politics, economy, culture, entertainment and new forms of storytelling. We’ve grown from a single Facebook page into a suite of digital products like website and into a newsletter.

Email: abcd@gmail.com

Logo